Oduu Haaraya

የኦሮሞ ህዝብ ከዚህ ብሄራዊ ውርደት መውጣት አለበት!

mararaa mana murtii
*******************************************************************

ዶ/ር መረራን በእደዚህ አይነት ሁኔታ ማየት ለኦሮሞ ህዝብ ብሔራዊ ውርደት ነው። ይህ የሚያመለክተው የኦሮሞ ህዝብ አንድ ያልተሻገረውና መሻገር ያለበት ትልቅ ድልድይ አለ። እርሱም አንድ የፓለቲካ ማህበረሰብ መሆን ነው።

አንድ ህዝብ የፓላቲካ ማህበረሰብ የሚሆነው ሶስት ዋና ዋና ነገሮችን ስያሟለ ነው።

1ኛ፣ አንደኛውና የአንድ ህዝብ ተቀዳሚ ተግባሩ ልጆች ወልዶ ማሳድግና መሪዎቹን ከውጭ ጥቃት መከላከል መቻል ነው። ልጆቹንና መሪዎቹን ከውጭ ጥቃት መከላከል ብቻ ሳይሆን ጥቃት ለማድረስ የሚያስብ አካል ከለ ከፍተኛ ዋጋ የሚያስከፍል ወይም ጦርነት የሚያስነሳ መሆኑን ተገንዝቦ ዋጋውን ቁጭ ብሎ እንዲተምን የሚያስገድድ የተፈራና የተከበረ ህዝብ ሲሆን ነው። በርካታ የአለም ትላልቅ ጦርነቶች የተነሱት ህዝቦች ራሳቸውን ከዚህ መሰል ጥጋበኞች ለመከላከል ሲሉ ነው።

ሌሎች ልጆቹን እና መሪዎችን በዘፈቀደ በሚገሉበት፣ በሚያስሩበት፣ ከሰፈለጋቸውም የራሳቸው ባሪያ ልያደርጉ በሚችሉበት ሁኔታ የፓለቲካ መህበረሰብ መሆን ብሎ ነገር የለም፣ እንደዚህ አይነት ህዝብ ለራሱ አስከብራለው ብሎ የሚያወራው ሌላ መብት የለውም። ካለን አይደለ ስለሌላ የምንናገረው?

2ኛ፣ አንድ ህዝብ የፓላቲካ ማህበረሰብ ሆነ የሚበለው የራሱን መሬትና የግዛት አንድነት ማስከበርና መጠበቅ ስቺል ነው። መሬት ያሌላው ህዝብ አገር የለውም።

3ኛ፣ አንድ ህዝብ የፓላቲካ ማህበረሰብ ሆነ የሚባለው የጋራ ሃብቱና የማንነት መገለጫ የሆኑትን ቋንቋውን እና ባህሉን ጠብቆ በዚያ ቋንቋና ባህል መኖርና ራሱን ማስተዳዳር ሲቺል ነው። ኣሳ ከውሃ ውጭ መኖር እንደማይችል ሁሉ አንድ ህዝብ ቋንቋውንና ባህሉን ጠብቆ በዚያ ውስጥ ከልኖረ የሞተ ህዝብ ነው። የኦሮምኛ የፌዴራል የሥራ ቋንቋ መሆን ከዚህ ውጭ ሌላ ትርጉም የለውም።

የዚህ ትውልድ የኦሮሞ ህዝብና የኦሮሞ ወጣቶች ግንበር ቀደም አላማና ተልእኮም የኦሮሞ ህዝብን ወደ አንድ የፓለቲካ ማህበረሰብ ማሻጋገርና የኦሮሞ ህዝብን በቀዬው በኦሮሚያና በከተማው በአዲስ አበባ ላይ አባ ወራ፣ በአገሩ በኢትዮጵያ ላይ በለአገርና ባለቤት ማድረግ ነው።

እዚህ ላይ ሁሉም መገንዘብ ያለበትና ፉፁም ልስተው የማይገባ እውነታ በእነዚህ ሶስት ዋና ዋና ብሄራዊ ጉዳዮች ላይ በኦሮሞ ህዝብ መካከል የፓለቲካ፣ የሃይማኖት ወይም የአከባቢ ልዩነት ያሌለ መሆኑን ነው።

የኦሮሚኛ ቋንቋ ሃይማኖት፣ ወይም ክልል፣ ወይም የፓላቲካ አስተሳሰብ የለውም። የኦሮሞ ህዝብ የጋራ ሃብት ነው።

የኦሮሞ ህዝብ መሬት ሃይማኖት፣ ወይም ክልል፣ ወይም የፓላቲካ አስተሳሰብ የለውም። የኦሮሞ ህዝብ ሁሉ የጋራ መኖርያውና በጋራ የሚጠብቀው የጋራ ሃብት ነው።

ለነዚህ ሶስት አላማዎች በመቆማቸው የሚፈሰው የኦሮሞ ልጆች ደምና የሚወረዱት የኦሮሞ መሪዎች ሃይማኖት፣ ወይም ክልል፣ ወይም የፓላቲካ አስተሳሰብ የላቸውም። ህዝባችን በጋራ ልጠብቃቸውና ዘብ ሊቆምላቸው የሚገቡ የኦሮሞ ህዝብ ልጆችና መሪዎች ናቸው።

ስለዚህ የኦሮሞ ህዝብ: ህዝብ ሆኖ ለመቀጠል፣ የሞቱትን ልጆቹንና መሪዎቹን አልቅሶ ከመቅበር አልፎ በሃይማኖት፣ በፓለቲካ አስተሳሰብ፣ እና በአከባቢ ሳይለያይ አንድ የፓለቲካ ማህበረሰብ ሆኖ በህይወት ላሉት ልጆቹና መሪዎቹ ደህንነትና ክብር መቆም አለበት።

የኦሮሞ ወጣቶችም ግንባር ቀደም ሥራና ምናልባትም ብቸኛው ኃላፊነት ይኸው መሆን አለበት። ምክንያቱም እነዚህ ሶስቱ ዋና ዋና የህዝባችን የህልውና ምሰሶዎች (በተቀመጡበት ቅደም ተከተል) ካሌሉ ሌላው ሁሉ የለም።

Check Also

loogii ethio telecom

Dhaabbanni Itiyoo-telekoom olaantummaa dhalattoota saba tokkoo qofaan kan dhuunftameedha

Ragaan sanadaa loogummaa fi olaantummaa dhalattoota saba tokkootiin dhuunfatamuu Itiyoo-telekoom saaxilu OMN harka seenuu itti …

One comment

  1. Galatoomi!! Salphina kana waarri nutti fidan waayyaanee otoo hintaane warra waraana oromoo mooraati naqee tikeetiin jijjiirratee diinaa kennee karaa boolee samsonaitii ofii qabate baye dha. Salphinni gaafa sanaa salphanne hamma har’aatti nu hordofaa jira!! Oromoon Oromia jiraatan garaa garummaa siyaasaa tokko hinqabani. Kan suummii saba orommootti ta’e ilmaanuma oromoo biyya alaa jiran qofa. Kanaaf namoonni akka kee salphinni saba isaa ittii dhaga’amu waan biraa dhiisanii wal barbaadanii waraana bilisummaa sabaa ijaarrachuu irraat bobba’uu qabu. Ani karaa mataa koo lubbuu tokkitii qabullee saba kanaaf gumaachuuf qophii dha.